-->
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለትራንዚት አጭር ቆይታ የሚያደርጉ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ተጓዦቹን የቢላሉል ሐበሺ ሙዚየምን እንዲጎበኙ አደረገ፡፡
=============================
ሙዚየም የታሪካዊ ውጤት አሻራ… ፣ የማህበራዊ እሴት… የጥበብ ዘመን ነጸብራቅ፣ በተናጠል ወይም በጥቅል በአንድ ተቋም ለእይታ፣ ለጥናትና ምርምር የሚቀርብበት ዘርፍ ነው፡፡ ቢላሉል ሐበሺ ሙዚየም የሙስሊሙን ታሪካዊ አሻራ በማሰባሰብ የማገዙ ትጋቱ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል፡፡ ይህ የቢላሉል ሐበሺ ሙዚየም ለሀገሪቱም የቱሪስት መዳረሻ ሆኖ በመደጋገፍ ሀገራዊው ፋይዳውም ላቅ ያለ ሆኗል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድም ለትራንዚት አጭር ቆይታ የሚያደርጉ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ተጓዦቹን በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ታሪካዊ ቦታዎችን ከሚያስጎበኛቸው መካከል አንዱ ቢላሉል ሐበሺ ሙዚየም ነው፡፡ በዚህ መሰረት የውጭ ዜጎች የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ቅርስ አሰባስቦ የያዘው ቢላሉል ሐበሺ ሙዚየምን ጎበኝተዋል፡፡
ይህ ሙዚየም የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ቅርስ እና መገለጫዎችን ሰንዶ የያዘ ሲሆን በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ሚና የነበራቸው ታላላቅ ኡለሞችና ታዋቂ ሰዎች ምስል፣ አልባሳታቸው፣ ሲጠቀሙበት የነበረ ቁሳቁሶች፣ ታሪካዊ ሰነዶችና ባህላዊ እቃዎች ይገኙበታል፡፡
Hayu Hayuna, Huzeyfa Sultan and 338 others
17 comments
47 shares
Like
Comment
Share

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለትራንዚት አጭር ቆይታ የሚያደርጉ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ተጓዦቹን የቢላሉል ሐበሺ ሙዚየምን እንዲጎበኙ አደረገ፡፡

Client Name
: bilalul habeshi
Service
: Islamic Museum
Start Date
: 7 October, 2022
End Date
: 9 October, 2022
Status
: Completed