-->

ሐጂ አብዱላዋሲዕ ዩሱፍ ከቤተሰቦቻቸው ያገኙትን ታሪካዊ የሆኑ ቅርሶችን ለቢላሉል ሐበሺ ሙዚየም አበርከቱ፡፡
==============================
በኢትዮጵያ የእስልምና ታሪክ ሁለተኛውን መፅሐፍ በመጻፍ ጨምር በበርካታ መጽሐፍት የደራሲነት ሥራዎቻቸው የሚታወቁት የሕግ አማካሪው ሐጂ አብዱልዋሲዕ ዩሱፍ የቅርስነት ይዘት ያላቸውን ጥንታዊ መፅሀፍትን ነው ለቢላሉ ሐበሺ ሙዝየም በስጦታ ያበረከቱት።
140 ዓመት ዕድሜ ያለው ጥንታዊ ቁርዓንን ጨምሮ በርካታ መጽሀፍትን ሙዚየሙ በአንድ ማዕከል ለህዝብ እይታ እንዲያውለው ማበርከታቸውን ሐጂ አብዱልዋሲዕ ዩሱፍ ህዳር 26፣2013 ለሙዝየሙ ባስረከቡበት ወቅት ተናግረዋል።

የቢላሉል ሐበሺ ሙዝየምን ከጎበኙ በኋላ “የመጽሐፉን አያያዝና ስርአቱን ስመለከት እኔ ጋር የሚቀመጡ ቅርሶች እዚህ መጥተው ቢቀመጡ የተሻለ አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ ይችላሉ” በሚል እሳቤ መጽሃፍቱን ለሙዝየሙ በስጦታ እንዳበረከቱ አስረድተዋል፡፡

የመጽሃፍ ስጦታውን የተረከቡት የቢላሉል ሐበሺ መስራች ኡስታዝ ሰዒድ ዐሊ በያን እንዳሉት ሐጂ አብዱልዋሲዕ ዩሱፍ በኢትዮጵያ የሙስሊሞች ታሪክ ያበረከቱት ሚና ታላቅነትን በማውሳት ፣ከቤተሶቦቻቸው ያገኙትንና የእርሳቸውን ጭምር የቅርስነት ይዘት ያላቸው መጽሐፍትን በማበርከታቸው ሙዚየሙ የቆመለተን ግብ ለማሳከት የጀመረውን ጥረት የሚያግዝ ነው፤ለአስተዋጽኦዋቸውም በቢላሉል ሸበሺ ስም አመስግነዋል።

የቢላሉል ሐበሺ ሙዚየም ዓላማው ቅርሶችን ከመላው ኢትዮጵያ መሰብሰብና፣ ለእይታ ማስተዋወቅ፣ ለጥናትና ምርምር እንዲውሉ ማድረግ ነው፡፡

ሐጂ አብዱላዋሲዕ ዩሱፍ ከቤተሰቦቻቸው ያገኙትን ታሪካዊ የሆኑ ቅርሶችን ለቢላሉል ሐበሺ የማህበረሰብ ሙዚየም አበርከቱ፡፡

Client Name
: bilalul habeshi
Service
: Islamic Museum
Start Date
: 9 October, 2022
End Date
: 9 October, 2022
Status
: In Progress